|
ነገረ ቅዱሳን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
«መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው» /መዝ. ፹፮፥፩/
በትራክት መልክ የተዘጋጀውን መልእክት ለማግኘት እዚህ ይጫኑ 
Click here to find the message about the Nativity of our Lady 
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ማኅበረ ቅዱሳን
ማሩ አይምረር፤ ወተቱ አይጥቆር
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
“ማኅበረ ቅዱሳን”
ሚያዚያ 24/2004 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ተዋቅሮ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፈቃድ አገልግሎቱን ከጀመረ እነሆ ሃያ ዓመታት ተቆጠሩ። ምንም እንኳን ማኅበሩን በራሳቸው ፈቃደኝነት የተሰባሰቡ ኦርቶዶክሳውያን ቢመሠርቱትም የማኅበሩ መሠረታዊ ዓላማ ግን ቤተ ክርስቲያን ተልእኮዋን ለማሳካት በምታከናውናቸው ተግባራት የልጅነት ድርሻውን ለመወጣት በመሆኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር በመግባት መተዳደሪያ ደንቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተቀመጠለት ተግባርና ሓላፊነት መሠረት አገልግሎቱን እያከናወነ ያለ ማኅበር ነው። አባላቱም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገራት በቤተ ክርስቲያኗ አጥቢያዎች በሚገኙ ሰበካ ጉባኤያት እና ሰንበት ት/ቤቶች ተመዝግበው የሚጠበቅባቸውን ክርስቲያናዊ ግዴታ እየተወጡ ይገኛሉ። እነዚህ አባላት አብዛኛዎቹ ቤተ ክርስቲያናቸውን በገንዘብ፣ በዕውቀትና በጉልበት ለማገልገል በፈቃዳቸው ቃል የገቡ ቤተ ክርስቲያንና ሀገሪቷ ካሏት ልዩ ልዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው ቤተ ክርስቲያናቸውን አገራቸውንና ወገናቸውን በልዩ ልዩ ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ ናቸው።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ኅብረ ነገር
“እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ ወውእቱ ልዑል ሣረራ"
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ስብከተ ወንጌል
ትንሣኤ (በመልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን)
በአርዓያ ሥላሴ የተፈጠረው አዳም
አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ፍጥረታትን ለተከታታይ አምስት ቀናት ከፈጠሩ በኋላ በስድስተኛው ቀን /ዓርብ/ በነግህ እንዲህ አሉ። ‹‹ንግበር ሰብአ በአርዓያነ ወበአምሳሊነ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር›› /ዘፍ ፩፥፳፮/። ሥላሴ በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ማለታቸው እንዴት ነው ቢሉ ሥላሴ ለባውያን፣ ነባብያን፣ ሕያዋን ናቸው። አዳምም ለባዊ፣ ነባቢ፣ ሕያው ነው። ሥላሴ ፍጹም መልክእ እንዳላቸው አዳምም ፍጹም መልክእ አለው። ሥላሴ በልብ በቃል፣ በእስትንፋስ ይመሰላሉ ለሰውም ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ አለው። ሥላሴ በባሕርያቸው የሚገዙትን አዳም በጸጋ እንዲገዛ ሥልጣን ሰጥተውታል።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ስብከተ ወንጌል
ቆሮንቶስ የግሪክ ከተማ ናት። ከአቴናም 75 ኪ.ሜ. ያህል ትርቃለች። በአዲስ ኪዳን ዘመን ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች የሚኖሩባት ትልቅ ከተማ ነበረች። አቀማመጧ በሁለቱ የግሪክ አውራጃዎች በመቄዶንያና በአካይያ መካከል በሚገኘው ልሳነ ምድር ነበረ።
ከተማይቱ የተመሠረተችው በባሕር መገናኛ ላይ በመሆኑ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለሚመጡ መርከቦች ምቹ ወደብ ነበረች። ከዚህም የተነሣ ንግድ እየደራባት ሄደ። ከተማይቱም እጅግ ተለወጠች። የከተማይቱ ነዋሪዎች የሚያመልኩት አፍሮዳይቲ የምትባለዋን የፍቅር አምላክ ነበር። «ቆሮንቶሳዊ» መባል የስድብ ስም እስኪሆን ድረስ የዝሙት ኃጢአት በከተማይቱ በዛ። አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ግሪኮች ሲሆኑ ብዙ ሮማውያንና አይሁዶች ይኖሩባት ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|